Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች አማኑኤል ኤርቦ በ70ኛው እና 86ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በበላይነት መምራት ጀምሯል።

በተመሳሳይ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ወልቂጤ ከተማና ሃድያ ሆሳዕና በድሬዳዋ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ 0 ለ 0 ተጠናቅቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.