Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ከፓሪሱ ኦሊምፒክ በፊት ተኩስ አቁም እንዲደረግ ለሩሲያ ጥያቄ ልታቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ ከፓሪሱ ኦሊምፒክ ቀደም ብሎ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ለሩሲያ ጥያቄ ልታቀርብ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታወቁ፡፡

የ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ ከፈረንጆቹ ሐምሌ 26 እስከ ነሐሴ 11 በፈረንሳይ ይካሄዳል፡፡

ይህን ተከትሎም የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከመጀመራቸው በፊት በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ተኩስ አቁም እንዲደረግ እንደሚጠይቁ ፕሬዚዳንት ማክሮን ገልጸዋል፡፡

እንደ አርቲ ዘገባ÷ ፕሬዚዳንቱ “ለሩሲያ የምናቀርበዋው የሰላም መልዕክት ይኖራል፤ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እንጠይቃለን፤ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴም የሚሰጠውን ውሳኔ እንከተላለን” ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የሩሲያ እና ቤላሩስ አትሌቶች በማንኛውም ዓለም አቀፋዊ የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፉ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል፡፡

ካለፈው ዓመት ጀምሮ ማዕቀቡን ለማሻሻል ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱን የገለጸው ኮሚቴው÷  የሩሲያ እና ቤላሩስ አትሌቶች የሀገራቸውን ባንዲራ ሳይዙ በግል የሚሳተፉበትን ዕድል ሊሰጥ እንደሚችል አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.