Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ዋር ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ጄነራል መኮንኖችና ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በተለያዩ በአጭር የትምህርት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ጀነራል መኮንኖችና ከፍተኛ መኮንኖች አስመርቋል።

በምርቃት ሥነ- ሥርዓቱ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት÷ መከላከያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን እንዲሆን የለውጥ ሥራዎች ተግባራዊ ተደርገዋል።

ከለውጡ በኋላ ሰራዊቱን ለመገንባት በተሰሩ ሥራዎች የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት የማያስደፍር ጀግና ሰራዊት መገንባት ተችሏል ብለዋል።

ጦርነት ሳይንስ ነው፤ አካባቢያዊና ቀጣናዊ ጉዳዮችን መገንዘብ ይጠይቃል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ÷ እንደ ሀገር የተሰጠውን ሃላፊነት በብቃት የሚወጣ ሰራዊት መገንባት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለምርቃት የበቁ የሰራዊቱ አመራሮች የጨበጡትን እውቀት በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም የማስከበር ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት።

የክብር እንግዶቹ መከላከያ ዋር ኮሌጅ፣ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና መሰረተ ልማቶች ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.