Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያስገነባውን የኢኖቬሽን ማዕከል አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ድጋፍ ያስገነባውን (ኢኖቪስ ኬ ኢትዮጵያ) የተሰኘውን የኢኖቬሽን ማዕከል አስመርቋል፡፡

ማዕከሉ በአይሲቲ ፓርክ ውስጥ የተገነባ ሲሆን÷ ለስታርት አፖችና በኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣት የሥራ ፈጣሪዎች በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መሰረተ ልማት ታግዘው ለሚከናወኑ ተግባራት አጋዥ ማዕከል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴዔታ ባይሳ በዳዳ÷ ማዕከሉ በዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ውስጥ የራሱን ድርሻ እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡

በተለይ ሥራ ፈጣሪ ባለሙያዎች የስታርትአፕ ሐሳቦችን ለማበልጸግ የላቀ ሚና እንዳለው ነው የተናገሩት፡፡

የኮይካ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶንግ ሆ ኪም በበኩላቸው÷ ኮይካ በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.