Fana: At a Speed of Life!

ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር በተለይም በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከ4 ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
• ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከባሻወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ እና ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.