Fana: At a Speed of Life!

የዐቢይና የረመዳን አጽዋማትን ምክንያት በማድረግ የጋራ የጸሎትና ኢፍጣር መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዐቢይ እና የረመዳን አጽዋማትን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የጋራ የጸሎትና አፍጥር መርሐ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የሐይማኖት አባቶች፣ የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ እምነት ተከታዮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ለሀገር ሰላምና አንድነት ጸሎት ተደርጓል።

በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ መርሐ ግብሩ ፍቅርን፣ አንድነትና አብሮነትን የበለጠ ለማጠናከር ታልሞ የተዘጋጀ ነው።

ከሚያለያዩን ይልቅ አንድ የሚያደርጉን መሰረቶች ይበዛሉ ያሉት ከንቲባዋ ÷ መሰረቶችን ይበልጥ ማስፋት እና ማጎልበት ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ቤተ እምነቶች ስለሰላምና ፍቅር በመስበክ ሚናቸውን ሲወጡ መቆየታቸውን ጠቅሰው ÷ አሁንም አንድ የሚያደርጉ መሰረቶችን ለማጠናከር የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ይህንን ለማጠናከር በቀጣይ በጋራ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.