Fana: At a Speed of Life!

ፓኪስታን የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተሞክሮ ለመውሰድ ተስማማች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓኪስታን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ኢኒሼቲቭን ተሞክሮ ለመውሰድ መስማማቷን አስታወቀች፡፡

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ከፓኪስታን የአካባቢ ጥበቃ አስተባባሪ ሮሚና ከርሺድ አላም ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ጀማል በከር÷ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመቅረፍ በትብብር እንዲሰሩ አስተባባሪዋ የተጫወቱን ሚና አድንቀዋል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ሀገራቱ በዘርፉ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ እንደ ጎርፍ፣ የምግብ እጥረት እና ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት ከፓኪስታን ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡

ሮሚና ከርሺድ አላም በበኩላቸው÷ፓኪስታን የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ኢኒሼቲቭ በሀገሪቱ አምስት የተለያዩ ከተሞች እንደምትተገብር ተናግረዋል፡፡

የአየር ንበረት ለውጥ ዓለም አቀፋዊ ችግር መሆኑን የገለጹት አስተባባሪዋ÷ ችግሩን ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የፓኪስታን መንግስት የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ረገድ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ማስገንዘባቸውንም ፖኪስታን ኢን ዘ ወርልድ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.