Fana: At a Speed of Life!

አየር ኃይል ያሰለጠናቸውን ቪዥን 2035 የአየር መንገድ ሰልጣኞች እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ቪዥን 2035 የአየር መንገድ ሰልጣኞች በደማቅ ስነ ስርዓት በማሥመረቅ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በያዘው ዕቅድ መሠረት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቪዥን 2035 የተሰኙ የመጀመሪያ ዙር የአየር መንገድ የበረራ ሠልጣኞችን በሥነ-ልቦናና በአካል ብቃት አሠልጥኖ እያስመረቀ ይገኛል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ መሥፍን ጣሳው እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.