Fana: At a Speed of Life!

የጤና መረጃ ስርዓትን ዲጂታላይዝድ በማድረግ 4 ሺህ የጤና ተቋማትን በኔትወርክ ማስተሳሰር መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገሪቱን የጤና መረጃ ስርዓት ዲጂታላይዝድ ለማድረግ በተሰሩ ሰፋፊ ስራዎች 4 ሺህ የጤና ተቋማትን በኔትወርክ ማስተሳሰር መቻሉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና መረጃ ስርዓትን ለማሻሻል በተጀመረው “ዲኤችአይኤስ ቱ” መተግበሪያ አማካኝነት ባለፉት ሰባትና ስምንት ዓመታት አንድ ቢሊየን ያህል መረጃ መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።

‘በመረጃ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔ ለተሻለ የጤና ስርዓት’ በሚል ሀገር አቀፍ የጤና መረጃ ስርዓት ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

መድረኩ በሀገሪቱ በ”ዲኤችአይኤስ ቱ” መተግበሪያ የተከወኑ ስራዎች ላይ ውይይት የሚደረግበትና ለቀጣይ የቤት ስራ የሚሰጥበት ነው ተብሏል።

በጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ገመቺስ መልካሙ በወቅቱ እንዳሉት÷ የጤና መረጃ ስርዓትን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

በዚህም ወረቀት አልባ አገልግሎትን በሆስፒታሎች ማስጀመር መቻሉን እና 4 ሺህ የሚሆኑ የጤና ተቋማትንም በኔትወርክ የማስተሳሰር ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡

በሐይማኖት ኢያሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.