Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ341 ሚሊየን በላይ ችግኝ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከ341ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ቢሮ ሃላፊ አስራት ገብረማሪያም (ዶ/ር) (ኢ/ር)÷የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በክልሉ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በቢሮው አስተባባሪነት ብቻ ከ152 ሚሊየን በላይ ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የተፈጥሮ ሃብትና መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዘርፍ ሃላፊ አቶ ውብሸት ዘነበ በበኩላቸው÷በግብርና ዘርፍ ለዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ ልማት 189 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በ42 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የደንና የአግሮ ፎረስትሪ ችግኞች በማዘጋጀትና በመትከል በአየር ንብረት ለውጥ የሚደርሰውን ተፅዕኖ ከመቋቋም ባለፈ የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.