የሥነ-ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 52 አመራሮችና ሠራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከቀረቡ 95 ጥቆማዎች 36 አመራሮችና ሠራተኞች ጥፋተኛ መሆናቸው በመረጋገጡ እርምጃ መወሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የቀሪዎቹ ጉዳይ ደግሞ በዲሲፕሊን ኮሚቴ በመታየት ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም በ2015 በጀት ዓመት ጥቆማ ቀርቦባቸው እርምጃ ሳይወሰድባቸው በሂደት ላይ በሚገኙ ጉዳዮች ላይ ክትትል ተደርጎ በ16 አመራርሮችና ሠራተኞች ላይም አሥተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ብሏል ተቋሙ፡፡
በጠቃላይ ካለፈው በጀት ዓመት ተላልፈው በሂደት ላይ የነበሩ ጥቆማዎችን ጨምሮ በ52 የተለያዩ የሥነ-ምግባር ጥሰቶች 108 አመራሮችና ሠራተኞች ጥቆማ ቀርቦባቸዋል መባሉን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ከነዚህ መካከልም 17 የጽሑፍ፣ 31 የደመወዝ፣ 2 ስንብት፣ አንድ ሠራተኛ ከደረጃ የማንሳት እና አንድ ሠራተኛ ነጻ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የቀሪ 54 ሠራተኞችና ኃላፊዎች ጉዳይ ደግሞ በሂደት ላይ እንደሚገኝ ነው የተመላከተው፡፡