Fana: At a Speed of Life!

የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን የሚያደናቅፉ ችግሮችን ለመቅረፍ የጋራ ግንዛቤ መያዝ ይገባል- አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን የሚያደናቅፉ ችግሮችን ለመቅረፍ የጋራ ግንዛቤ መያዝ ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።

የምክር ቤቱ አባላት ከከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በሀገሪቱ አጠቃላይ የመንገድ መሰረተ ልማት ሂደት ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በህዝብ ውክልና ስራ ወቅት የምክር ቤቱ አባላት ከየምርጫ ክልላቸው የመንገድ መሰረተ ልማትን በሚመለከት የተነሱ ጥያቄዎች ላይ ነው ከሚኒስቴሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እያካሄዱ የሚገኙት፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ÷ በሀገሪቱ አጠቃላይ የመንገድ መሰረተ ልማት ዘርፍ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ በመወያየት የጋራ ግንዛቤ እንዲኖር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በዘርፉ መጠነ ሰፊ ስራዎች መከናወናቸውን መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የካሳ ክፍያን ጨምሮ የመንገድ ስራዎችን የሚያደናቅፉ ችግሮች ሲገጥሙ እንዴት መቅረፍ እንደሚቻል የጋራ ግንዛቤ መያዝ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.