Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ- ጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚቴ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ ጅቡቲ 16ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚቴ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በጅቡቲ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የሎጂስቲክስ እና ትራንስፖርት ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እና የጅቡቲ የመሠረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሁማድ ተገኝተዋል።

አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ÷መድረኩ በ16ኛው የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች አንዲሁም ከስምምነቱ በኋላ በተከሰቱ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መፍትሄዎችን ለማስቀመጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ስብሰባው በሁለቱ ሀገራት የትብብር ማዕቀፎች፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና በጠረፍ ላይ ንግድ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በዲኪል ጋላፊ መንገድ ግንባታ መጓተት ዙሪያ እና በመሰል አንገብጋቢ ነጥቦች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ኤምባሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.