በመዲናዋ ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት አውደ ርዕይና ባዛር ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት” ከተማ አቀፍ አውደ ርዕይና ባዛር ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል።
አውደ ርዕይና ባዛሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ በይፋ ከፍተዋል።
በባዛሩ ከ200 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን÷ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ ማኅበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገዛበትና የገበያ ትስስር የሚፈጥርበት ነው ተብሏል።
በጊዮን ሆቴል የተከፈተው አውደ ርዕይና ባዛር ለአራት ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተጠቁሟል፡፡