Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ3 ሰው ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 636 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 176 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ከዚህ ውስጥ 98 አዲስ አበባ፣ 33 አማራ ክልል፣ 31 ትግራይ ክልል፣ 7 ሶማሌ ክልል፣ 3 ኦሮሚያ ክልል፣ 2 ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ 2 አፋር ክልል ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ከ5 እስከ 90 የእድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን፥ 175 ኢትዮጵያውያን አንደኛው ደግሞ የውጭ ሃገር ዜጋ ነው።

ከዚህ ውስጥ 116ቱ ወንዶች ሲሆኑ፥ 60ዎቹ ሴቶች ናቸው።

በተያያዘም በትናንትናው እለት 3 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን፥ ሁለቱ ከአማራ ክልል አንደኛው ደግሞ ከአዲስ አበባ ከተማ ነው ተብሏል።

ይህም በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎችን ቁጥር 60 አድርሶታል።

በሌላ በኩል 75 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 620 ደርሷል።

እስካሁን በኢትዮጵያ ለ186 ሺህ 985 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሺህ 521 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

29 ሰዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና ክፍል ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.