የኦዲፒ አባላት በብልጽግና ፓርቲ አስፈላጊነት ዙሪያ በአዳማ ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 8፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) አባላት በብልጽግና ፓርቲ አስፈላጊነት ዙሪያ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ ለ 3 ቀናት ሲካሂዱት የነበረው ውይይት ተጠናቋል።
በውይይት መድርኩ ማጠናቀቂያ ስነ ስርዓት ላይም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የድርጅቱ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ተገኝተዋል።
በውይይት መድርኩ ከ2 ሺህ በላይ የድርጅት አባላት በብልጽግና ፓርቲ አስፈላጊነት ዙሪያ በጥልቀት መምከራቸው ተገልጿል።
ውይይቱ የብልጽግና ፓርቲን የወደፊት የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ የተጠናቀቀ መሆኑን ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።