Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከቻይና የጉሙሩክ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከቻይና የጉሙሩክ አስተዳደር ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅት ህገ ወጥ የንግድ ስርዓትን፣ የዕፅ ዝውውርን ለመቆጣጠር እንዲሁም የጉሙሩክ ስርዓትን ለማዘመንና የጉሙሩክ መረጃዎችን ለመለዋወጥ አንድ የቴክኒክ ኮሚቴ እንዲዋቀር መደረጉ ተገልጿል።

የቴክኒክ ኮሚቴ ቡድኑ አዲስ አበባ በመምጣት ከኢትዮጵያ ቡድን ጋር የኢትዮጵያን የጉሙሩክ አገልግሎት አሰጣጥ የሚጎበኝ ይሆናል።

ከዚህ ባለፈም የተለያዩ የቴክኖሎጂ አገልግሎት ድጋፎችን ለኢትዮጵያ ጉሙሩክ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፥ ለጉሙሩክ አገልግሎት ሰራተኞች የተለያዩ ስልጠናዎችን ይሰጣል ነው የተባለው።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያና ቻይና በኢዲስ አበባ የደረሱት ስምምነት የጉሙሩክ ትብብርን በማጠናከር በጉሙሩክ ስነ ስርዓት፣ በልዩ የጉሙሩክ ቀጠና፣ በስጋት አመራር፣ በህግ ማስከበር እና በኮንትሮባንድ ቁጥጥር የበለጠ በትብብር ለመስራት እንደሚያግዙ መግለጻቸው ይታወሳል።

ይህም ኢትዮጵያ እና ቻይና የጀመሩትን ትብብር ወደላቀ ደረጃ ያሸጋግራል መባሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.