ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።
ሹመቶቹ የሀገሪቱን የፀጥታ እና የደህንነት ብሎም የውጭ ግንኙነት አካላትን በማጠናከር የተጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ በብቃት ለመወጣት የተደረገ የአመራር ሽግሽግ ነው ተብሏል።
በዚህ መሰረትም
• አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣
• ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
• ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
• አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ድህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
• ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር
• አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።