ጁንታውን የህወሓት ቡድን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተካሄደ
በዚህም በጅማ፣ በአጋሮ፣በደሌ፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በጉጂ ዞን ጎሮ ዶላ ወረዳ፣በጂማ ዞን ጌራ ወረዳ እና በአርሲ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች የተካሄዱት ጁንታውን የህወሓት ቡድን የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በሰላም ተጠናቀዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ “የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን እንደግፋለን፣ ኦነግ ሸኔ እና ጽንፈኛው የሕወሓት ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ናቸው፣ በሕወሓት የጥፋት ኃይል ላይ እየተወሰደ ያለው ሕግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።