በአዳማ ከተማ ከትግራይ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዳማ ከተማ ነዋሪ ከሆኑ የትግራይ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።
በከተማዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ከከተማዋ ብልፅግና ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች ጋር እየወያዩ ነው።
የትግራይ ህዝብ እንደሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሃገር ህልውና ሲታገል የኖረ ሃገር ወዳድ ህዝብ መሆኑን የአዳማ ከተማ ብልፅግና ፅህፈት ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዱልጀሊል አብዱሮ ተናግረዋል።
የህውሃት ፅንፈኛ ቡድን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ታግሎ ወደ ስልጣን የመጣ ቢሆንም ባለፉት አመታት ግን የመከፋፈል አጀንዳዎችን ሲያሰርፅ እንደነበረ ተናግረዋል
ከዚህ ሲያልፍ እጅግ የበዛ መብት ጥሰትንም ሲያደርስ የቆየ መሆኑንም አንስተዋል።
በድርጅቱ ውስጥ ያሉ አካላትንም በውስጣዊም ሆነ በውጫዊ መንግድ ለመታገል ስራ ላይ የነበው ማእከላዊ ፌደራሊዝም ችግር የነበረበት መሆኑም አቶ አብዱልጀሊል ጠቁመዋል።
ከግለሰብ እስከ ክልል የራስን ሃብት በራስ የመምራት እና ባለቤት መሆን አለባቸው የሚለውንም መብት ሲጥስ የቆየ እና ጣልቃ ሲገባ መቆየቱም ገልፀዋል።
የሚተላለፉ የተለያዩ ውሳኔዎች ከህዝብ ጋር ውይይት የማይደረግባቸው እንደነበሩ ያነሱት አቶ አብዱልጀሊል በጥቂቶች ብቻ ሲመሩ የነበሩ አካሄዶች የህዝብ ቅሬታን እና ግጭቶችን ሲፈጥሩ እንደነበር ተናግረዋል።
ይህ ቡድን ለ20 አመታት የትግራይን ህዝብ የጠበቀን የመከላከያ ሃይል ማጥቃቱ ህዝቡን ማስቆጣቱ በመግለፅ ህዝቡ ከመከላከያ ጎን መሆኑ ቡድኑ በቀላሉ እንዲሸነፍ አድርጎታል ነው ያሉት።
አብሮ በመኖር ሃገርን መገንባት ይቻላል ያሉት ሃላፊው አብሮነትን ለማጠናከር ውይይቱ ወሳኝ መሆኑም ተነግሯል።
በይስማው አደራው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!