ጠ/ሚ ዐቢይ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ተወካዮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ተወካዮች ጋር ተወያዩ።
ከንግዱ ዘርፍ፣ ከሙያ ማኅበራት፣ ከሀይማኖት ተቋማት መሪዎች እና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከተወከሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ነው የተወያዩት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ግብዣ ነው በሀገሪቱ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመሪዎች ደረጃ እና ከተለያዩ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች የደቡብ አፍሪካ መንግስት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ጥረት ያደርጋሉም ነው የተባለው።
በተጨማሪም በነገው እለት በጆሃንስበርግ በስቴዲየም ከህዝቡ ጋር እንዲገናኙ ዝግጅት ተደርጓል።
በአልአዛር ታደለ