Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ተጓዦች የአሸኛኘት ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአድዋ ተጓዦች የአሸኛኘት ስነ ስርዓት ተካሄደ።

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተካሄደው የአሸኛኘት ስነ ስርዓት ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ  የአድዋ ተጓዦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ አባት እና እናት አርበኞች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በአሸኛኘት ስነ ስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ “ስለ አድዋ ሳሰብ ስሜታዊ እሆናለው ያንንም ስሜት የፈጠረብኝ የአባቶቼ የማሸነፍ ስሜት ነው” ብለዋል።

የሚሰማኝም ስሜት የማሸነፍ እና ሁልጊዜ የመራመድ ስሜት ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

አባቶቻችን እና እናቶቻችን ከኢትዮጵያ ጫፍ ጫፍ ተነስተው በጀግንነት ለፈተና ሄደው ፈተናውን አሸነፉ ያሉት ኢንጂነር ታከለ፥ አሁን ወደ አድዋ ሲሄዱ ሰላምን እና አንድነትን ለመስበክ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይሄኛው ፈተና ከባድ መሆኑን፤ መሞት ወይም መግደል ሳይሆን ልብን መማረክ እንደሆነ የገለፁት ምክትል ከንቲባው፥ በጉዟቸው በሚረግጧቸው በእያንዳንዱን የኢትዮጵያ መሬት ፍቅር እና አንድነትን ስበኩ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አድዋ ከማሸነፍ፣ ከሞመት እና ከመግደል ባለፈ አንድነት እና ፍቅር እንደሆነም ለዓለም አሳዩ ብለዋል።

የአድዋን ማእከል በአዲስ አበባ ከተማ የሁሉም ኢትዮጵያ ማእከል እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ ያለውን ሀብት አሰባስቦ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታውን እንደሚያጠናቅቅም ቃል ገብተዋል።

ጉዞ ወደ አድዋ የአድዋን ድል ለማሰብ ሲካሄድ ዘንድሮ  ለ7ኛ ጊዜ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.