የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
ምክር ቤቱ በጠዋቱ ውሎው በተወሰኑ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህም ቀደም ሲል ከነበሩ የወረዳዎች ቁጥር ከህዝቡ ጥያቄ በመንሳት ተጨማሪ አንድ ወረዳ ማለትም ሁንዱሉ ወረዳ እንዲደራጅ ውሳኔ አሳልፏል።
እንዲሁም በክልሉ የቀበሌ ቁጥር ከ474 ወደ 518 እንዲያድግ በሙሉ ድምፅ ማጽደቁን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጉባኤውም ከሰዓት የሚቀጥል ሲሆን፥ የክልሉ መንግስት የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት የመገምገምና በሌሎችም አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።