በትግራይ ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከር 369 ሺህ ዶላር ድጋፍ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በትግራይ ክልል በጥቃቅንና አነስተኛ የስራ ዘርፎች የተደራጁ 2ሺህ 500 ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከር የሚያግዝ 369ሺህ ዶላር ድጋፍ መገኘቱን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የከተሞች ምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ልማት ኤጀንሲ ገለጸ።
በክልሉ በነበረው ችግር ኪሳራ የደረሰባቸው ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ በማይጨው ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄዷል።
በዚህም ተጠቃሚ ከሚሆኑት መካከል በመቀሌ ሶስት ክፍለ ከተሞች እንዲሁም ማይጨው፣ አዲግራት፣ አብይ አዲ፣ አድዋ እና አክሱም ከተሞች ያሉት ኢንተርፕራይዞች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።
እያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ እስከ ሶስት ሰዎችን እንደሚይዝና ተጠናክረው በየተደራጁበት የስራ ዘርፍ በመሰማራት እራሳቸውን እንዲችሉ ድጋፍ ለማደረግ መታቀዱም ነው የተነገረው።
ድጋፉ የስራ አጥነት ችግር ለማቃለል ያግዛል መባሉን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!