ብሩንዲ ፕሬዚዳንቶቿ ስልጣን ሲለቁ 500 ሺህ ዶላር እና ቅንጡ ቤት አንዲሰጣቸው የሚያደርግ ውሳኔ አሳለፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ቡሩንዲ ለቀጣዩ ምርጫ እራሳቸውን ለማግለል ለወሰኑት ፕሬዚዳት ፔሬ ንኩሩንዚዛ የ500 ሺ ዶላር እና ቅንጡ ቤት እንዲሰጣቸው የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈች።
የቡሩንዲ ፓርላማ የሀገሪተቱ ፕሬዚዳንቶች ስልጣን ሲለቁ የ500ሺ ዶላር እና ቅንጡ ቤት እንዲሰጣቸው የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል።
ቡሩንዲ 2015 ህገ መንግስታዊ ቀውስ ባጋጣማት ወቅት ፕሬዚዳንት ንኩሩንዚዛ የሀገራቸውን ህገ መንግስት ድንጋጌ በመተላለፍ ለሶስተኛ ጊዜ በምርጫ መወዳደራቸው ይታወሳል።
ይህ እርምጃቸውም በሀገሪቱ ከፍተኛ ግጭት በማስነሳት በርካታ ሰዎች ለህልፈት እንዲዳረጉ ምክንያት ሆኗል።
በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ በሙስና እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ስማቸው በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ ከፈረንጆቹ 2020 በኋላ በስልጣን የመቆየት ፍላጎት እንደሌላቸው ያሳወቁ ሲሆን፥ ይህም በርካታ የሀገሬውን ዜጎች አስገርሟል።
ለዚህም ይመስላል የሃገሪቱ ፓርላማ የ500ሺ ዶላር እና ቅንጡ ቤት ለምግዛት ውሳኔ አስተላልፏል።
ለተሰናባቹ ፕሬዚዳንት የሚገነባው ቪላ ቤት መጠኑና ምን ያህል ወጪ እንደሚፈጅ በዘገባው አልተገለጸም።
ከስልጣን ለሚወርዱ ፕሬዚዳንቶች ተብሎ የጸደቀው ህግ እንደ ተመድ የአለም የምግብ ፕሮግራም 65 በመቶው በድህነት በሚኖርባት፣ 10 ሚሊየን ህዝብ ደግሞ የምግብ ዋስና ባልተረጋገጠባት ብሩንዲተገቢ አለመሆኑን ጠቁሟል።
ምንጭ፡- አልጀዚራ