Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተሸለሙ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሴቶች፣ ቤተሰብ እና ህጻናት ሚኒስቴር በየዓመቱ በፈርንጆቹ ሃምሌ 31 የሚከበረውን የፓን አፍሪካን የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ ለፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ሽልማት አበርክቷል።
በፕሮግራሙ ላይ ለሃገራቸው እና ለአፍሪካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ታዋቂ አፍሪካዊያን ሴቶች ሽልማት ተሰጥቷል።
በዚሁ ጊዜ በቀረበው ማብራሪያ ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ በተለያዩ የሙያ መስኮች በሃገር ውስጥ፣ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶችን ለማብቃትም ሆነ በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሽልማቱ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።
ሽልማቱንም በዲሞክራቲክ ኮንጐ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ ተቀብለዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ከፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በተጨማሪ፣ የቀድሞ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚ ሱሉሁ ሃሰን እንዲሁም በተለያዩ መስኮች አስተዋጽኦ ያበረከቱ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዜጎች ሽልማት እንደተበረከተላቸው ከፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.