Fana: At a Speed of Life!

አፍሪኸልዝ ኢቨንትስ በመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ላይ ከ1 ነጥብ 5ሚሊየን በላይ ማስክ በነፃ አሰራጭቷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪኸልዝ ኢቨንትስ በመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ላይ ከ1 ነጥብ 5ሚሊየን በላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ በነፃ ማሰራጨቱን አስታወቀ።

የተለያዩ በዓላትን ለኮቪድ ወረርሽኝ በማያጋልጥ ሁኔታ ማክበር ወቅቱ የሚጠይቀው ዋና ጉዳይ መሆኑም ተጠቁሟል።

አፍሪኸልዝ ኢቨንትስ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው÷
በመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ላይ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በነፃ አድሏል።

በሁለቱ በዓላት ላይ ከ10 ሚሊየን በላይ ለሚሆን ህዝብ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከያ መንገዶችን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠቱንም አስታውቋል።

ህብረተሰቡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ በአግባቡ እንዲጠቀም፣ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና ሳሙና እንዲታጠብ፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና ሳኒታይዘር በመጠቀም ራሱን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዲከላከል ትምህርት መስጠቱን በመግለጫው አመላክቷል።

የኮቪድ-19 ስርጭት በመስፋፋቱ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የህብረተሰቡ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን ማጠናከር አለበት ብሏል።

ዜጎች በቸልተኝነት ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ከኦሮሚያ ክልል፣ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር የ‘ሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ ሀርሰዴ’ የኢሬቻ በዓል ተንቀሳቃሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትና ነፃ የማስክ እደላ ማካሄዱን ጠቁሟል።

አፍሪኸልዝ ኢቨንትስ በመዲናዋ የተለያዩ ስፍራዎች በመዘዋወር፣ በመስቀልና በኢሬቻ በዓላት ዋዜማና በበዓሉ እለት የተሳካ ስራ ማከናወኑን ገልጿል።

በቀጣይም በአዲስ አበባና ወረርሸኙ እየተስፋፋባቸው በሚገኙ ከተሞች በመንቀሳቀስ የሄሎ ጤና (ሄሎ ፈያ) ‘8455’ የተሰኘ አጭር የስልክ መስመር በመጠቀም ከኮቪድ-19 ጋር የተገናኙና መሰል ጤና ነክ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሸ እንደሚያደርግም ታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.