Fana: At a Speed of Life!

አልማ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበበ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አልማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
አሸባሪው ህወሓት ባደረገው ወረራ የአማራ እና የአፋር ክልል ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በልዩ ልዩ መጠለያ ጣቢያዎች ለመኖር መገደዳቸው ይታወቃል፡፡
ወይዘሮ ንጋቷ ዘውዴና አቶ ስሜነህ አበሻ÷ በርካታ ድጋፎችን ሲያደረጉ መቆየታቸውን ጠቁመው÷ ድጋፉም ወደ ቀያቸው ተመልሰው እስኪቋቋሙ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡
ተፈናቃዮቹም በበኩላቸው ለሚደረግላቸው ድጋፍ አመስግነው÷ በድጋፍ ስርጭቱ በኩል የሚታዩ ውጣ ውረዶች እንዲስተካከሉ ጠይቀዋል፡፡
በዚህም ለሕጻናት፣ ለሚያጠቡ እናቶች እና ለነፍሰ ጡሮች የተለየ እንክብካቤ እና ድጋፍ ቢደረግላቸው÷ መንግሥት ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ቋጭቶ ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ በፍጥነት ቢመቻች የሚል አስተያየትና ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም በክፉ ቀን የሚደርስ ወገን ስላላቸው መኩራታቸውን ገልፀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.