ጠ/ ሚ ዐቢይ ተደምረው ለእውነት ለቆሙ ኢትዮጵያውያን እና የአፍሪካ ቀንድ ዳያስፖራዎች አድናቆታቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተደምረው ለእውነት ለቆሙ ኢትዮጵያውያን እና የአፍሪካ ቀንድ ዳያስፖራዎች አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉዳዩን አስመልክተው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷መደመር የመከፋፈል አጥሮችን ደርምሶ ወደ አንድነት መምጣት ነው ብለዋል፡፡
ባለፉት 3 ዓመታት ባደረግናቸው የቀጠናዊ ውሕደት ጥረቶች የሕዝብ ለሕዝብ ትሥሥር ወሳኝ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
ተደምረው ለእውነት ለቆሙ ኢትዮጵያውያን እና የአፍሪካ ቀንድ ዳያስፖራዎችም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ #በቃ