Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የአትሌት ድርቤ ወልተጂ የ1 ማይል ርቀት ክብረወሰን ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ድርቤ ወልተጂ የአንድ ማይል ርቀት ክብረወሰን በአለምአቀፉ  አትሌቲክስ እውቅና አግኝቷል። ለመጀመሪያ ጊዜ በላቲቪያ ሪጋ በ1 ማይል ርቀት በተካሄደው የሴቶች ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ4 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ከ98 ማይክሮ ሰከንድ  በመግባት የርቀቱን ክብረወሰን ማሻሻሏ የሚታወስ ነው።
Read More...

የብራዚሉ ክለብ ሳንቶስ ከ111 ዓመት በኋላ ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን መውረዱ አነጋጋሪ ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ ከዋክብቶችን ያፈራው የብራዚሉ ክለብ ሳንቶስ ከ111 ዓመት በኋላ ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን መውረዱ ደጋፊዎችን አስቆጥቷል፡፡ ሳንቶስ የክለቡ ወርቃማ ዘመን በተባለው  1950ዎቹ እና 60ዎቹ 12 የሀገራዊ ውድድር ክብሮችን፣6 የሊግ ውድድር ዋንጫዎችን እንዲሁም 2 የኮፓሊቨርታዶርስ ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል፡፡ ይሁን…

ኢትዮጵያ በውሃ ዋና ስፖርት ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በውሃ ዋና ስፖርት ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች፡፡ የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ስፖርት ብሔራዊ ቡድን በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 8ኛው የዞን 3 አፍሪካ ውሃ ዋና ሻምፒዮና በማስተርስ ዋና ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግቧል፡፡ ኢትዮጵያ በዞን 3 የአፍሪካ…

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በማስመልከት በጂግጂጋ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በጂግጂጋ ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡ በወንዶች በተደረገው የሩጫ ውድድር ከጅግጅጋ አትሌቲክስ ፕሮጀክት የተወከለው አትሌት አሕመድ መሐመድ 1ኛ፣ ከጅግጅጋ አትሌቲክስ ፕሮጀክት የተወከሉት አትሌት በረከት መሐመድ 2ኛ እንዲሁም…

ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለቦች ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ላይ ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ 100 እና 75 ሺህ እንዲቀጡ መወሰኑን የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በ6ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ከዳኞች እና…

በፕሪሚየር ሊጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በዛሬው እለት ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ የመጀመሪያው ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የአዳማ ከተማ ግቦችን ሀቢብ መሐመድ እና ቢንያም አይተን ሲያስቆጥሩ÷አንተነህ ተፈራ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ ጎል…

ሊቨርፑልና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳቸው የተጫወቱት ሊቨርፑልና ቼልሲ ድል ቀናቸው። ብራይተንን ያስተናገደው ቼልሲ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል። በተመሳሳይ በሜዳው የተጫወተው ሊቨርፑል ፉልሃምን አስተናግዶ 4 ለ 3 አሸንፏል። በርንማውዝ አስቶቪላን አስተናግዶ 2 ለ2 ሲለያይ፤…