Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ ዛሬ በ3 የማጣሪያ ውድድሮች ትሳተፋለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውን ሴቶች አትሌቶች የሚሳተፉበት የ800 ሜትር፣ 5 ሺህ ሜትር እንዲሁም 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ይካሄዳል፡፡ ከረፋዱ 5፡05 ላይ የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ፣ ምሽት 2፡02 ላይ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ እንዲሁም ምሽት 2፡53 ላይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ይካሄዳል፡፡ በ800 ሜትር የማጣሪያ ውድድሩ ÷ አትሌት ሀብታም ዓለሙ፣ አትሌት ወርቅነሽ መለሰ እና አትሌት ትዕግስት ግርማ ይሳተፋሉ፡፡ እንዲሁም በ5 ሺህ ሜትር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ አትሌት መዲና…
Read More...

ኢትዮጵያ የምትካፈልባቸው 2 የፍጻሜ ውድድሮች ምሽት ላይ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምትካፈልባቸው የሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር እና የወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሠናክል የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ምሽት ላይ ይካሄዳሉ፡፡ ምሽት 4፡31 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ ይጠበቃሉ፡፡ እንዲሁም ምሽት 4፡42 ላይ በሚካሄደው የወንዶች 3…

በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ 3ኛ ደረጃን ይዛለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው 19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ በ4 ሜዳሊያዎች 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች አሜሪካ በ3 ወርቅ፣ 2 ነሃስ እና በአንድ ብር ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ ስፔን በሁለት የወርቅ ሜዳሊያ 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡…

በወንዶች 10 ሺህ ሜትር አትሌት ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳልያ አስገኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በውድድሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቋል። ውድድሩን ዩጋንዳዊው አትአትሌት ጆሹዋ ቼፕቴጌ 1ኛ በመሆን አጠናቋል።

ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ በ1 ሺህ 500 ሜትር ለፍፃሜ አለፉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌት ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወደ ፍፃሜ አለፉ፡፡ አትሌት ብርቄ ኃየሎም ርቀቱን በ4 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ ከ46 ማይክሮ ሰከንድ 2ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ማለፏን ስታረጋግጥ በተመሳሳይ ከምድብ ሁለት ድርቤ ወልተጂም 3 ደቂቃ ከ55…

ስፔን የ2023 የሴቶች የዓለም ዋንጫን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023 የሴቶች የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔን እንግሊዝን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን አንስታለች። የቡድኑ አምበል ኦልጋ ካርሞና በ29ኛው ደቂቃ ለስፔን የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥራለች። የእንግሊዟ ግብ ጠባቂ ሜሪ ኢርፕስ በሁለተኛው አጋማሽ የጄኒፈር ሄርሞሶን ፍፁም ቅጣት ምት አድናለች።…

ኢትዮጵያውያን የሚጠበቁበት የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍጻሜ ውድድር ምሽት 1፡25 ላይ ይካሄዳል፡፡ በውድድሩ÷ አትሌት በሪሁ አረጋዊ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ይስማው ድሉ ተጠባቂ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ቀን 12፡05 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ሂሩት መሸሻ፣ ድርቤ ወልተጂ…