Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሻሸመኔ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መመለሱን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሻሸመኔ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማን ሽንፈት ተከትሎ ከ15 የውድድር ዘመናት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መመለሱን አረጋግጧል፡፡ ሻሸመኔ ከተማ ለመጨረሻ ጊዜ በሀገሪቱ ትልቁ ሊግ ተሳትፎ ያደረገው በ2000 ሚድሮክ ሚሌኒየም ፕሪሚየር ሊግ ላይ ነበር።
Read More...

የእርምጃ ተወዳዳሪው አትሌት ምስጋና ዋቁማ ለሀገሩ ወርቅ አስገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛምቢያ እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 ዓመት በታች የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ምስጋና ዋቁማ ወርቅ አገኘች፡፡ አትሌት ምስጋና ዋቁማ በ10 ሺህ ሜትር የእርምጃ ውድድር አንደኛ ሆኖ በማጠናቀቁ ነው ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው፡፡ በዛምቢያ ንዶላ የአፍሪካ ከ20 እና ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና…

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2015 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2015 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግን ለተከታታይ ሦስተኛ ጊዜ አሸንፏል። በ25 ሳምንት የሊጉ መርሃግብር ይርጋጨፌ ቡናን የገጠመው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሎዛ አበራ ሃትሪክ እና በመሳይ ተመስገን አንድ ግብ 4 ለ 0 በመርታት አንድ ጨዋታዎች እየቀረው የሊጉ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።…

በፕሪሚየርሊጉ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ በሊጉ ተጣባቂ የነበረው የፋሲል ከነማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ በፋሲል ከነማ 2 ለ 1 አሸነፊነት ተጠናቋል፡፡ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ…

በዛምቢያ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በዛምቢያ ንዶላ እየተካሄደ ባለው ከ20 ዓመት በታች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ውድድር ዛሬ የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር  ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል። በዚህም አትሌት ውብርስት አስቻለ በአንደኝነት የወርቅ ሜዳሊያ…

ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ፡፡ ለኢትዮጵያ ቡና መስፍን ታፈሰ፣ ሮቤል ተክለሚካኤል፣ አንተነህ ተፈራ እና አማኑኤል ዮሐንስ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ብቸኛዋን የድሬዳዋ ጎል ያሲን ጀማል አስቆጥሯል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 30 በማድረስ ከሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ ጋር…

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ21ኛ ሣምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ፡፡ 9፡00 ላይ አርባምንጭ ከተማን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ በእስማኤል ኦሮ አጉሮ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ፈረሰኞቹ ከተከታያቸው ባሕርዳር ከተማ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሥድስት ማስፋት…