Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ 3ኛ ደረጃን ይዛለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው 19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ በ4 ሜዳሊያዎች 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች አሜሪካ በ3 ወርቅ፣ 2 ነሃስ እና በአንድ ብር ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ ስፔን በሁለት የወርቅ ሜዳሊያ 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ በሁለቱ ቀናት ውድድር ኢትዮጵያ 1 ወርቅ ፣1 ነሃስ እና 2 ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ከዓለም ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዛ ትገኛለች፡፡…
Read More...

በወንዶች 10 ሺህ ሜትር አትሌት ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳልያ አስገኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በውድድሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቋል። ውድድሩን ዩጋንዳዊው አትአትሌት ጆሹዋ ቼፕቴጌ 1ኛ በመሆን አጠናቋል።

ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ በ1 ሺህ 500 ሜትር ለፍፃሜ አለፉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌት ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወደ ፍፃሜ አለፉ፡፡ አትሌት ብርቄ ኃየሎም ርቀቱን በ4 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ ከ46 ማይክሮ ሰከንድ 2ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ማለፏን ስታረጋግጥ በተመሳሳይ ከምድብ ሁለት ድርቤ ወልተጂም 3 ደቂቃ ከ55…

ስፔን የ2023 የሴቶች የዓለም ዋንጫን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023 የሴቶች የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔን እንግሊዝን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን አንስታለች። የቡድኑ አምበል ኦልጋ ካርሞና በ29ኛው ደቂቃ ለስፔን የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥራለች። የእንግሊዟ ግብ ጠባቂ ሜሪ ኢርፕስ በሁለተኛው አጋማሽ የጄኒፈር ሄርሞሶን ፍፁም ቅጣት ምት አድናለች።…

ኢትዮጵያውያን የሚጠበቁበት የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍጻሜ ውድድር ምሽት 1፡25 ላይ ይካሄዳል፡፡ በውድድሩ÷ አትሌት በሪሁ አረጋዊ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ይስማው ድሉ ተጠባቂ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ቀን 12፡05 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ሂሩት መሸሻ፣ ድርቤ ወልተጂ…

ባሕርዳር ከተማ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከአዛም ጋር ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በካፍ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ባሕርዳር ከተማ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከታንዛንያው አዛም ክለብ ጋር ያካሂዳል። ጨዋታው ከቀኑ 10 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል። በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚሰለጥነው ባሕርዳር ከተማ÷ ለጨዋታው በባሕርዳር እና አዲስ አበባ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል።…

ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ የወርቅ፣ ብርና ነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡዳፔስት የአለም  የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የወርቅ፣ የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አስገኙ። በሀንጋሪ እየተካሄደ ባለው  የ19ኛው የአለም  የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በመጀመሪያው ቀን የ10 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር ተካሂዷል። በውድድሩም ጉዳፍ ፀጋይ 1ኛ፣ ለተሰንበት…