Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ለተሰጣት እውቅና የእንኳን ደስ ያለሽ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በሃንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 54ኛው የዓለም አትሌቲክስ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ላበረከተችው አስተዋጽኦ ለተሰጣት የ”ፕላክ ኦፍ ሜሪት” እውቅና የእንኳን ደስ ያለሽ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዚዳንቷ በመልዕክታቸው÷ “ውድ ደራርቱ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአትሌቲክስ ላደረግሽው የላቀ አስተዋጽኦ ለተሰጠሽ እውቅና እንኳን ደስ አለሽ” ብለዋል። “ለዚህ መብቃትሽ ለስፖርቱ ያለሽን የማያወላውል…
Read More...

ዛሬ ምሽት በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ በሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ምሽት በሚካሄደው የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለአሸናፊነትከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። በውድድሩ በአሜሪካ ኦሬጎን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርቀቱ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው አትሌት ለተሰንበት…

በ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ በሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ። በምድብ አንድ የተወዳደረው አትሌት ጌትነት ዋለ 8:19.99 በሆነ ሰዓት በመግባት ከምድቡ 1ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ውድድር ማለፍ ችሏል። በምድብ ሶስት…

19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቡዳፔስት ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሀንጋሪ ቡዳፔስት በዛሬው ዕለት ይጀመራል፡፡ በውድድሩ የመጀመሪያ ቀን በ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ወንዶች ማጣሪያ ለሜቻ ግርማ፣ ጌትነት ዋለ እና አብርሃም ስሜ ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ፡፡ በተጨማሪም በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ሒሩት መሸሻ፣ ብርቄ ሃየሎም…

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት ላበረከተችው አስተዋፅኦ እውቅና ተሰጣት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት ላበረከተችው አስተዋፅኦ የ”ፕላክ ኦፍ ሜሪት” ሽልማት እና እውቅና ተበርክቶላታል፡፡ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ በአትሌቲክስ ዘርፍ የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ያስጠራች ድንቅ አትሌት ስትሆን÷ አሁን ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገለች…

ቲዎ ዋልኮት ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአርሰናል እና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የክንፍ ተጫዋች ቲዎ ዋልኮት በ34 ዓመቱ ከፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋችነት ራሱን አግልሏል፡፡ ዋልኮት ለልጅነት ክለቡ አርሰናል ከ100 በላይ ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን በእግር ኳስ ህይወቱ 47 የእንግሊዝ ብህራዊ ቡድን ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል፡፡ በ16 ዓመቱ አርሴናልን…

አማኑኤል ገብረሚካኤል ፋሲል ከነማን በይፋ ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የመቀሌ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል ፋሲል ከነማን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረውን ኮንትራት ያጠናቀቀው አጥቂው እስከ 2017 ዓ.ም በሚያቆይ ኮንትራት ለፋሲል ከነማ መፈረሙን ክለቡ አስታውቋል፡፡ አማኑኤ ገብረ ሚካኤል ከዚህ በፊት በዳሽን ቢራ፣ በሰሜን ሸዋ…