Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
 
ምክር ቤቱ የተወያየባቸውና ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦
 
ምክር ቤቱ በቀዳሚነት የተወያየው የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣንን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባራትን ለመወሰን በቀረበው ደንብ ላይ ሲሆን÷ የፌዴራል መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 የነዳጅና ኢነርጂ ጉዳዮችን የሚመራ ተቋም በአዲስ መልከ ያቋቋመ መሆኑን ተከትሎ ባለስልጣኑ ሴክተሩን በብቃት መምራት የሚያስችል ስልጣንና ተግባር እንዲኖረው የሚያስችል ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምከር ቤት ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
 
በመቀጠል ምክር ቤቱ ውይይቱን ያደረገው የብሔራዊ የክፍያ ስርዓት አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡
 
ቀደም ሲል የነበረውን አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት አገራችን በጀመረችው አጠቃላይ አገራዊ የሪፎርም አጀንዳ ማዕቀፍ ውስጥ የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎችን ተሳትፎ በማስፋት የክፍያ ስርዓቱን ውጤታማነት፣ አስተማማኝነትና ተወዳዳሪነት ለማጎልበት፣ ገበያው አበከሮ የሚፈልጋቸውንና በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉትን ለውጦች፣ ዕድገቶችና መሻሻሎች ታሳቢ ባደረገ መልኩ የክፍያ ስርዓታችንን ማዘመን ይቻል ዘንድ የማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
 
ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው ከጣሊያን ሪTብሊክ መንግስት ለጤናው ዘርፍ ዘላቂ የልማት ግቦች ፕሮጀክት እንዲሁም ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ በተፈቀዱ ብድሮች ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡
 
ከጣሊያን መንግሥት የተገኘው ብድር 10 ሚሊየን ዩሮ ሲሆን፥ ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር የተገኘው ብድር ደግሞ 400 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡
 
ምክር ቤቱም ብድሮቹ ከ 1 ፐርሰንት ያነሰ ወለድ የሚከፈልባቸው፣ እስከ 12 ዓመታት የሚደርስ የችሮታ ጊዜ ያላቸው እና በ38 ዓመታት ተከፍለው የሚጠናቀቁ መሆናቸውን፥ ይህም ከአገራችን የብድር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋገጥ ይጸድቁ ዘንድ ረቂቅ አዋጆቹን ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡
 
ምክር ቤቱ በአራተኛ ደረጃ ውይይቱን ያደረገው የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡
 
በካፒታል እጥረት ምክንያት የስራ እንቅስቃሴያቸው የተዳከሙ ድርጅቶች ተጨማሪ ካፒታል ለማሰባሰብ ከሚሸጡት አዲስ አክሲዮን የሚገኝ ገቢን ከግብር ነጻ ማድረግ የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደዚሁም በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 65 (2) ኢኮኖሚያዊ አስተዳደራዊ ወይም ማህበራዊ ምክንያቶች መኖራቸው ሲታመን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በማውጣት አንድን ገቢ ከግብር ነፃ ሊያደርግ እንደሚችል በተደነገገው መሰረት ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
 
ሌላው ምከር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ለማስከፈል የቀረበ ረቂቅ ደንብ ነው፡፡
 
ወደ አገር በሚገቡ በተወሰኑ ምቶች ላይ አነስተኛ ቀረጥ በመጣል በሚገኘው ገቢ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በማስፋፋት፤በመጠገን እና በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስቻል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
በመጨረሻም ምክር ቤቱ የመንግስትና የግል አጋርነት አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ የተወያየ ሲሆን÷ የመንግስትና የግል አጋርነት አሰራር በዋናነት የግል ሴከተሩን እውቀት፣ ክህሎትና የፋይናንስ አቅም በመጠቀም የህዝብ አገልግሎት መሰረተ ልማቶችን ጥራትና ደረጃ ለማሳደግና ለማስፋፋት፣ ስራው በግልጽ ውድድና ፍትሃዊት እንዲፈጸም ለማድረግ እንዲሁም በአገራችን ማክሮ ኢኮኖሚሂደት የሚታዩ ተግዳሮቶችን በተለይም የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ችግን እንዲታደግ ለማድረግ እንደ አንድ የልማት ፋይናንስ አማራጭ ዘዴ በመውሰድ የተቀየሰ የህግ ማዕቀፍ ነው፡፡
 
የተቀሰውን ዓላማ ለማሳከት ከተያዩ ሀገራት መንግሥታት ጋር በሚኖር የኢኮኖሚዲፕሎማሲ አማካኝነት እንዲሁም ከውጭ ባለሀብቶች ጋር በሚደረግ ግንኙነት ለአገር እና ለሕዝብ ጠቀሜታ ያላቸው የፕሮጀክት ሀሳቦችን በቀጥታ ድርድር መተግበር ጠቃሚ መሆኑ የታመነበት ቢሆንም አሁን በስራ ላይ ያለው አዋጅ ይህን አሰራC የማይፈቅድ በሆኑ አዋጁን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኗል፡፡
 
ምክር ቤቱም በረቂቅ የማሻሻያ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተካዮች ምክር ቤት መርቶታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.