የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ ÷ ተቋሙ በተሟላ የስልጠና ማዕከል ውስጥ ከፍተኛ አመራሮችን እያሰለጠነ ነው ብለዋል፡፡
ይህንንም በአፍሪካ ደረጃ በማሳደግ የአህጉሩን መሪዎች አቅም በማጎልበት የአፍሪካን ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡:
አካዳሚው ከስልጠና በተጨማሪ በምርምርና ማማከር አገልግሎት ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን÷ በቅርቡም የፓን አፍሪካኒዝም ፎረም እንደሚያዘጋጅ ተጠቅሷል፡፡
በጉብኝቱ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍስሀ ሻውልን ጨምሮ የአካዳሚው ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።