Fana: At a Speed of Life!

ለወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ቡድን  ከ43 ሚሊየን ብር  በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ለሆነው የወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ቡድን  ከ43 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ፡፡

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ቡድን  የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር  በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተካሄዷል።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ገብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ÷ ስፖርት ለሰላም ፣ለፍቅር ፣ለጤና እና  ለአንድነት ጉልህ ድርሻ አለው ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ቡድንም የማህበረሰቡን አንድነት ፣ባህልና ታሪክ በመጠበቅ በገጽታ ግንባታ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝም  ገልፀዋል።

ቡድኑ ስለ ደመወዝሳይሆን ስለ ጨዋታ ብቻ ማሰብ አለበት ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ  ÷ ቡድኑ የሁሉም አምባሳደር በመሆኑ ማህበረሰቡ የገንዘብ  ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን  የጉራጌ  ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.