Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሕብረትና የአውሮፓ ሕብረት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት እና የአውሮፓ ሕብረት በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር አላማ ያደረገ ከፍተኛ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በምክክሩ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የጤና፣ የሰብዓዊ ጉዳዮችና ማህበራዊ ልማት ኮሚሽነር ሚናታ ሳማቴ ሴሱማ እና የአውሮፓ ሕብረት የጤናና የምግብ ደህንነት ኮሚሽነር ስቴላ ኪሪያኪዲስ ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል አመራሮች፣ የቤልጂየም የልማት ትብብርና የዋና ከተሞች ሚኒስትር ካሮሊን ጄኔዝ፣ የአፍሪካ ሕብረትና የአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገራት ተወካዮችም ተሳትፈዋል፡፡

ምክክሩን ያዘጋጁት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የጤና፣ የሰብአዊ ጉዳዮችና ማህበራዊ ልማት ክፍልና የአውሮፓ ሕብረት ናቸው ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ሕብረትና የአውሮፓ ሕብረት በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ትብብር ማጠናከር፣ የአፍሪካና የአውሮፓ የጤና ስርዓቶችን አቅም መገንባትና ሁለቱ ወገኖች በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ማጎልበት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እንደሚወያዩ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ከውይይቱ በኋላ የአፍሪካ ሕብረትና የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን በርካታ የባለብዙ መስኮች የትብብር ስምምነቶች ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.