የኢትዮ-ጂቡቲ የዲፕሎማሲ ወዳጅነት አውደ ርዕይ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጂቡቲ 127ኛ የዲፕሎማሲ ወዳጅነት አውደ ርዕይ በይፋ ተከፍቷል፡፡
በመክፈቻው ላይም የምሥራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም የጂቡቲ የንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር ዩሱፍ ሙሳን ጨምሮ ሌሎች የጂቡቲ የሥራ ኃላፊዎች እና አምባሳደሮች መገኘታቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡