የአማራ ክልል ም/ቤት የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አነሳ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ም/ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የሁለት ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የ154 የወረዳ ረዳት ዳኞችን ሹመት በማጽደቅ መጠናቀቁን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡