Fana: At a Speed of Life!

ፌደራል ፖሊስ 139 የእሳት አደጋ መንስኤዎችን በፎረንሲክ አጣርቶ ውጤት ይፋ ማድረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባለፉት ስድስት ወራት የደረሱ 139 የእሳት አደጋ መንስኤችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ፌደራል ፖሊስ ለጠያቂው አካል የፎረንሲክ ምርመራዎችን በማድረግ ለፍትሕ መረጋገጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገልጿል።

ባለፉት ስድስት ወራትም በሀገር አቀፍ ደረጃ የደረሱትን የእሳት አደጋ መንስኤዎች በዘመናዊ የፎረንሲክ መሣሪያ ለይቶ ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረትም በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር ምክንያት 73፣ በመካኒካል ችግር ምክንያት 19፣ ኢንሹራንስ ለማግኘት 15፣ በቸልተኝነት 15 እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች 8 አደጋዎች እንደደረሱ ተጠቁሟል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ከደረሱ 139 የእሳት አደጋዎች ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ 130 አደጋዎች እንደተከሰቱ የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

የእሳት አደጋ ከደረሰ ጉዳቱን ለመቀነስ ማጥፋት ተገቢ ቢሆንም ከጠፋ በኋላ ግን መረጃው እንዳይጠፋ ቦታው ሳይነካካ ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል።

ቃጠሎው በፎረንሲክ ምርመራ እስካልተረጋገጠ ድረስ የደረሰው በዚህ ምክንያት ነው ብሎ መፈረጅ አስቸጋሪ ሲሆን÷ ፍረጃው የፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድርም ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.