Fana: At a Speed of Life!

5 የአውሮፕላን ማረፊያዎችን እየገነባሁ ነው- የኢትዮጵያ አየር መንገድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አምስት ተጨማሪ የሀገር ውስጥ መዳረሻ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን እየገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እንዳሉት÷ አየር መንገዱ አሁን ላይ 136 ዓለም አቀፍ እንዲሁም 22 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት፡፡

በአሁኑ ወቅት በሚዛን ቴፒ አማን፣ ነጌሌ ቦረና፣ ያቤሎ፣ ጎሬ መቱ እና ደብረ ማርቆስ ከተሞች አምስት የሀገር ውስጥ መዳረሻ የአውሮፕላን ማረፊያ እየገነቡ መሆናቸው ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህ መካከልም አራቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ይህም በሀገር ውስጥ ያሉ ደንበኞችን ፍላጎት ተከትሎ የሚተገበር መሆኑን አመላክተው÷ በቀጣይም ሌሎች መዳረሻዎች ጥናት ላይ በተመሠረተ መልኩ ግንባታ የሚቀጥል ይሆናል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ጉዳት የደረሰባቸው የአክሱምና የቀብሪደሃር አውሮፕላን ማረፊያዎች እድሳት እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰው÷ በቅርቡ ወደ ሥራ ይገባሉ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2035 ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ለማድረግና በዓመት 67 ሚሊየን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ራዕይ አስቀምጦ እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.