Fana: At a Speed of Life!

በየካቲት ወር 33 ሺህ 711 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት በየካቲት ወር ብቻ 33 ሺህ 711 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የገጠር ከተሞችን እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወነ ሥራም በየካቲት ወር 11 ከተሞችና መንደሮችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም 142 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር መካከለኛ መስመር እና 174 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር ዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ የተካሄደ ሲሆን÷ 45 ትራንስፎርመሮች መተከላቸውም ተጠቁሟል፡፡

እስከ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስም የተቋሙ አጠቃላይ ደንበኞች ቁጥር 4 ሚሊየን 615 ሺህ 787 መድረሱ ተገልጿል።

ከእነዚህ ውስጥም 3 ሚሊየን 725 ሺህ 500 ያህሉ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ መሆናቸውን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.