Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ድል መታሰቢያ የአውቶቡስ ተርሚናልና የዓድዋ ፕላዛዎች ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል መታሰቢያ የአውቶቡስ ተርሚናል እና የዓድዋ ፕላዛዎች ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

ተርሚናሉ ተገልጋዮችን ከፀሐይና ዝናብ ከመታደግ ባሻገር የተሳፋሪዎችን ደኅንነት የበለጠ ለማስጠበቅ የሚያስችል የደኅነት ካሜራ የተገጠመለትና የሰዎች ማረፊያ የተካተተበት መሆኑን የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብራርተዋል፡፡

ፕላዛዎቹም የአዲስ አበባ ነዋሪ ምን ያህል የጋራ መገልገያዎችና መዝናኛዎችን እንደሚፈልግ የሚያመለክት ብሎም የሕዝብን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

በክፍያ ወደሚገባባቸው የመዝናኛ ቦታዎች ከፍለው መግባት የማይችሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማችን ነዋሪዎች እንደዚህ ባሉ የጋራ መገልገያ ቦታዎች መዝናናት እና መገልገል ሲችሉ መመልከት ደስ እንደሚያሰኝም ገልጸዋል፡፡

በኮሪደር ልማት የሕዝባችንን ከፍተኛ ፍላጎት በመገንዘብ በርካታ ፕላዛዎችን፣ መዝናኛዎችን፣ የአውቶቡስና የታክሲ ተርሚናሎችን እንዲሁም ፓርኪንጎችን አካትተን በመሥራት ላይ እንገኛለን ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.