ሀገር የጣለችብንን አደራ በሀቀኝነት እንወጣለን-የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የምርጫ አስፈፃሚ ወጣቶች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ሀገር የጣለችብንን አደራ በሀቀኝነት እንወጣለን ሲሉ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የምርጫ አስፈፃሚ ወጣቶች ተናገሩ።
ነገ በሚካሄደው 6 ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ከ135 ሽህ በላይ ዜጎች በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ድምፃቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሁለት የምርጫ ክልሎች 121 የምርጫ ጣቢያዎች በእያንዳንዱ አምስት የምርጫ አስፈፃሚዎች ተመድበዋል።
ለፍና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስተያየታቸውን ከሰጡ ምርጫ አስፈፃሚዎች መካከል÷ ወጣት ሄኖክ አበበ እና ወጣት አሳምነው መስፍን ለምርጫው ሂደት እና አፈፃፀም በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዪ ስልጠናዎችን ወስደናል ብለዋል።
ሀገሪቱ የጣለችብን ታላቅ ሀላፊነት በታማኝነት እና በሀቀኝነት እንሰራለንም ነው ያሉት ።
ወጣቶቹ በምርጫው ሂደት ከድምፅ አሰጣጡ እስከ ድምፅ ቆጠራው ብሎም እስከ ወጤት ገለፃው ድረስ በትኩረት እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል።
በለሚኩራ 12 የፖለቲካ ፖርቲዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11 የፖለቲካ ፖርቲዎች ደግሞ ለክልል ምክር ቤት በነገው ምርጫ እጩዎቻቸውን አቅርበዋል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
5
Engagements
Boost Post
5