Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ መድን እና ሀዲያ ሆሳዕና ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተካሔዱ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ መድን እና ሀዲያ ሆሳዕና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፍዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ሀዲያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን ዳግም ንጉሴ በ33ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል አሸንፏል፡፡ በሌላ የ11ኛ ሣምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ደግሞ ኢትዮጵያ መድን ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡ የኢትዮጵያ መድንን ጎሎች ሀቢብ ከማል በ44ኛው እና ያሬድ ዳርዛ በ89ኛው እንዲሁም የወልቂጤ ከተማን ብቸኛ ጎል ጌታነህ ከበደ በ75ኛው ደቂቃ…
Read More...

በፕሪሚየርሊጉ የተጫዋቾች ዝውውር የሚካሄድበት ቀን ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ሕዳር 29፣2015 (ኤፍ  ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ የ2015 ዓ.ም አጋማሽ የተጫዋቾች ዝውውር የሚካሄድበት ቀን ይፋ ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት የውድድር አመቱ አጋማሽ  ዝውውር ከታህሳስ 18 እስከ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ሉዊስ ኤነሪኬ ከስፔን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ተሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ህዳር 29፣2015 (ኤፍ ቢሲ) ሉዊስ ኤነሪኬ ከስፔን ብሄራዊ አሰልጣኝነታቸው መሰናበታቸውን የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ስፔን በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በሞሮኮ በመለያ ምት መሸንፏን ተክትሎ ነው ፌዴሬሽኑ ሉዊስ ኤነሪኬን ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነቱ የተሰናበተው። አሰልጣኙ እና የቡድን አጋሮቻቸው ብሄራዊ ቡድኑን በመምራት ላበረከቱት አስተዋፅኦ…

የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሣምንት ጨዋታ የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ጎሎች ኢብራሂም ከድር በ60ኛው እንዲሁም ናትናኤል ሰለሞን በ74ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡ የአርባምንጭ ከተማን ጎሎች ደግሞ አሕመድ ሁሴን በ3ኛው እና አላዛር…

ኤደን ሀዛርድ ከቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን በሪያል ማድሪድ እየተጫወተ የሚገኘው ኤደን ሀዛርድ ከቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል፡፡ ቤልጂየም በጊዜ ከዓለም ዋንጫው መሰናበቷን ተከትሎ ነው ኤደን ሀዛርድ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ያገለለው፡፡ የ31 ዓመቱ ሀዛርድ ለሀገሩ በ126 ጨዋታዎች ተሰልፎ 33 ጎሎችን ማስቆጠሩን ጎል ዶት ኮም ዘግቧል፡፡…

የክርስቲያኖ ሮናልዶ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ አለመግባት አዳዲስ የፖርቹጋል ኮከቦችን አስተዋውቋል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊዘርላንዱ ጨዋታ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ አለመግባቱ አዳዲስ የፖርቹጋል ኮከቦች በመድረኩ እንዲታወቁ እድል ሰጥቷል፡፡ ትላንት ምሽት ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን 6 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታ አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ተጠባባቂ ወንበር ላይ በማስቀመጥ በምትኩ የቤኔፊካውን አጥቂ ጎንዛሎ ራሞስን…

ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን በሰፊ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች። ምሽት አራት ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን 6ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች። ለፖርቹጋል ጎንሳሎ ራሞሰ በ17ኛው ፡ በ51ኛውና በ67ኛው ደቂቃዎች ላይ ባስቆጠራቸው ጎሎች ሃትሪክ ሲሰራ ቀሪዎቹን ሶስት ጎሎች ደግሞ ፔፔ በ33ኛው ፥ ራፋኤል…