Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በዓለም ዋንጫው ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ዋንጫው የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ። ኔዘርላንድስ ከአሜሪካ እንዲሁም አርጀንቲና ከአውስትራሊያ የዛሬ ጥሎ ማለፍ መርሐ ግብሮች ናቸው። ቀድም ብሎ በሚካሄደው ጨዋታ ምድብ 1ን በቀዳሚነት የጨረሰችው ኔዘርላንድስ ከምድብ 2 ሁለተኛ በመሆን ካጠናቀቀችው አሜሪካ ጋር ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ትጫወታለች። የምድብ ሶስቷ አርጀንቲና ደግሞ በምድብ አራት ፈረንሳይን ተከትላ ካለፈችው አውስትራሊያ ጋር ትገናኛለች። የሁለቱ ጨዋታ አሸናፊዎች ሕዳር 30 ቀን ግማሽ ፍጻሜውን…
Read More...

ስዊዘርላንድ ብራዚልን ተከትላ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) - ስዊዘርላንድ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጠች። ምሽት አራት ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ስዊዘርላንድ ሰርቢያን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች። ከምድቧ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን ቀድማ ያረጋገጠችው ብራዚል በካሜሩን 1ለ0 ብትሸነፍም የምድቡ መሪ ሆና አጠናቃለች። ስዊዘርላንድ ደግሞ ሁለተኛ…

በዓለም ዋንጫው ደቡብ ኮሪያ ጥሎ ማለፉን ስትቀላቀል ጋና ከዓለም ዋንጫው ተሰናብታለች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው ደቡብ ኮሪያ ፖርቹጋልን ተከትላ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች። በምድብ 8 ማምሻውን 12 ሰአት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደቡብ ኮሪያ ፖርቹጋልን 2 ለ 1 በማሸነፍ በ4 ነጥብ በግብ ክፍያ ጥሎ ማለፉብን ተቀላቅላለች። በምድቡ ሌላኛው ጨዋታ አፍሪካዊቷ የምድቡ ተወካይ ጋና በዑራጋይ 2 ለ 0 ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው…

በዛሬው የዓለም ዋንጫ ሁለት የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበትን ጨምሮ አራት ጨዋታዎች ይካሔዳሉ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ ከምድብ ሰባት እና ስምንት ወደ ጥሎ ማለፍ የሚቀላቀሉ ቡድኖችን ለመለየት የሚደረጉ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡ በዚሁ መሰረት በምድብ ሰባት የተደለደለችው ብራዚል ቀድማ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን ብታረጋግጥም የምድቧን ሶስተኛ ጨዋታ ከአፍሪካዊቷ ካሜሮን ጋር ምሽት አራት ሰዓት ላይ ታደርጋለች፡፡ በዚሁ…

የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡ ቤልጂየም በ22ኛው የዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፉን ሳትቀላቀል መቅረቷን ተከትሎ ነው አሰልጣኙ ከኃላፊነታቸው የለቀቁት፡፡ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ቤልጂየም ካናዳን 1 ለ 0 ብታሸንፍም÷ በሞሮኮ 2 ለ 0 በመሸነፏ እና ወደ…

ሞሮኮ እና ክሮሺያ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍቢ ሲ) አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ካናዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ እና ክሮሺያ ያለምንም ግብ ከቤልጂየም ጋር አቻ በመለያየት ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል፡፡ ሞሮኮ ከምድቧ 7 ነጥብ በመያዝ በቀዳሚነት እንዲሁም ክሮሺያ ደግሞ አምስት ነጥብ በመያዝ ነው ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉት፡፡ በኳታር አስተናጋጅነት እየተካሔደ በሚገኘው 22ኛው የዓለም ዋንጫ…

በዛሬው የዓለም ዋንጫ ጀርመን ከኮስታሪካ የምታደርገው ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ ዛሬ ከምድብ አምስት እና ስድስት ወደ ጥሎ ማለፉ የሚቀላቀሉ ቡድኖችን የሚለዩ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡ በዚህም መሰረት በምድብ አምስት ጀርመን ከኮስታሪካ ምሽት አራት ሰዓት ላይ የሚደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት በዚሁ ምድብ ጃፓን ከስፔን…