Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አርጀንቲና የዓለም ዋንጫ ቆይታዋን የሚወስነውን ወሳኝ ጨዋታ ምሽት ታደርጋለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታሩ ዓለም ዋንጫ ዛሬ የምድብ ሦስት እና አራት የመጨረሻ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡ በምድብ አራት ቱኒዚያ ከፈረንሳይ እንዲሁም አውስትራሊያ ከዴንማርክ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በምድብ አራት ፈረንሳይ ስድስት ነጥብ በመያዝ ከምድቡ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፏን አስቀድማ ስታረጋግጥ አውስትራሊያ ሦስት ቱኒዚያ እና ዴንማርክ ደግሞ በ1 ነጥብ ይዘው የምሽቱን ጨዋታ ያካሂዳሉ። በተመሳሳይ ከምድብ ሦስት ሳዑዲ አረቢያ ከሜክሲኮ እና ፖላንድ ከአርጀንቲና ምሽት አራት ሰዓት ላይ…
Read More...

በዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ  ሴኔጋል  እና ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ ምሽት 12 ሰዓት ኔዘርላንድስ ከኳታር እንዲሁም ሴኔጋል ከኢኳዶር ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ በጨዋታው አፍሪካዊቷ ሴኔጋል  ኢኳዶርን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ኔዘርላንድስ ኳታርን 2 ለ 0 አሸንፋለች፡፡ በዚህም ሴኔጋል እና ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን…

የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ኢራን እና አሜሪካ ከ24 ዓመታት በኋላ በዓለም ዋንጫ ዛሬ ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ኢራን እና አሜሪካ ከ24 ዓመታት በኋላ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በዛሬው ዕለት ይፋለማሉ፡፡ በምድብ ሁለት የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ አያቶላዎቹ ኢራን እና የፖለቲካ ባላንጣዋ አሜሪካ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በአል ቱማማ ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ በ1998 ፈረንሳይ…

 ብራዚል ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋገጠች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ ብራዚል እና ስዊዘርላንድ ምሽት ላይ የምድብ ሁለት ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡ በዚህም ብራዚል ስዊዘርላንድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በምድቡ ያላትን ነጥብ ወደ ስድስት ከፍ አድርጋለች፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ከፈረንሳይ በመቀጠል ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች ሁለተኛ ሀገር መሆን ችላለች፡፡ የብራዚልን…

አዝናኙ የካሜሩን እና የሰርቢያ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ድራማዊ ትዕይንት ያስተናገደው የካሜሩን እና የሰርቢያ ጨዋታ 3 አቻ ተጠናቋል፡፡ በጨዋታው ካሜሩን በሰርቢያ ብልጫ ተወስዶባት 3 ለ 1 ስትመራ ብትቆይም በቪንሰንት አቡበከር እና ቺፖ ሞቲንግ ሁለት ጎሎች ታግዛ አቻ መሆን ችላለች። የካሜሩንን ጎሎች ጄን ካሴሌቶ፣ ቪንሰንት አቡበከር እና ቺፖ ሞቲንግ ሲያስቆጥሩ የሰርቢያን…

የሊጉ መርሐ ግብሮች እና ተስተካካይ ጨዋታዎች በድሬዳዋ መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ11ኛ እስከ 13ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎችን ጨምሮ ተስተካካይ ጨዋታዎች በድሬዳዋ መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ፡፡ የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ሳምንት በባህር ዳር ከተማ የተከናወነ ሲሆን ከ6ኛ እስከ 10ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በድሬደዋ ከተማ እየተካሄደ…

በዛሬው የዓለም ዋንጫ ሁለት የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበትን ጨምሮ አራት ጨዋታዎች ይካሔዳሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘጠነኛ ቀኑን በያዘው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ውሎ ካሜሮን እና ጋና የሚሳተፉበትን ጨምሮ አራት ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡ በዚሁ መሰረት በምድብ ሰባት የተደለደሉት አፍሪካዊቷ ካሜሮን እና ሰርቢያ ቀን ሰባት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡ በዚሁ ምድብ የተደለደሉት ብራዚል እና ስዊዘርላንድ ደግሞ ምሽት አንድ ሰዓት ላይ…