Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ስፔንና ጀርመን አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) - የምድባቸውን ሁለተኛ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ያደረጉት ስፔንና ጀርመን ሳይሸናነፉ ቀርተዋል። ሁለቱ ቡድኖች 90 ደቂቃውን 1ለ1 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል። ውጤቱን ተከትሎ ጀርመን በአንድ ነጠብ በምድቧ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ስፔን በአንፃሩ በ4 ነጥብ ምድቡን አየመራች ትገኛለች። በዚህ ምድብ ሚገኙት ጃፓንና ኮስታሪካ እኩል ሶስት ነጥብ አላቸው። ጀርመን የምድቧን የመጀመሪያ ጨዋት በሽንፈት የጀመረች ሲሆን ስፔን በአንፃሩ በሰፊ ጎል ልዩነት ማሸነፏ የሚታወስ ነው።
Read More...

ካናዳ ከኳታሩ የዓለም ዋንጫ ተሰናበተች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ካናዳ በክሮሺያ 4 ለ 1 መሸነፏን ተከትሎ ከውድድሩ ሁለተኛዋ ተሰናባች ሀገር ሆናለች። የካናዳው አልፎንሶ ዴቪስ በዛሬው ጨዋታ ክሮሺያ ላይ በ2ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ፈጣኗ ጎል ሆና ተመዝግባለች። ከዚህ ቀደም የኔዘርላንድሱ ኮዲ ጋክፖ በ6ኛው ደቂቃ የውድድሩን ፈጣን ጎል…

ተጠባቂው የስፔን እና ጀርመን ጨዋታ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት ስፔን ከጀርመን የሚያደርጉት የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡ በምድብ አምስት የተደለደሉት ሁለቱ ሀገራት ከምድብ ለማለፍ ምሽት 4 ሰዓት በኳታሩ አል ባይት ስታዲየም ፍልሚያቸውን ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ ኮስታሪካን በሰፊ ውጤት ያሸነፈችው ስፔን በጊዜ ከምድቡ ለማለፍ ጨዋታዋን የምታደርግ ሲሆን÷…

በዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ወሳኝ የምድብ ድሏን አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ቤልጂየምን 2 ለ 0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች፡፡ በጨዋታው ብርቱ ተፎካካሪ ሆና የቀረበችው የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ከእረፍት መልስ አብዱልሃሚድ ሳብሪል እና ዛካሪያ አቡክላል ባስቆጠሯቸው ጎሎች ቤልጂየምን በማሸነፍ ወሳኝ ድል አስመዝግባለች፡፡ ሞሮኮ ከሴኔጋል በመቀጠል…

በዛሬው የዓለም ዋንጫ ውሎ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ ሲቀጥል አራት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታወች ይከናወናሉ፡፡ በዚሁ መሰረት በምድብ አምስት የተደለደሉት ጃፓን እና ኮስታሪካ ቀን 7 ሰዓት ላይ እንዲሁም በእዚሁ ምድብ የሚገኙት ስፔን ከጀርመን ምሽት አራት ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡ በዛሬ የጨዋታ መርሐ ግብር በምድብ ሥድስት የሚገኙት…

ፈረንሳይ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የኳታር የዓለም ዋንጫ ምሽት ላይ ፈረንሳይ እና ዴንማርክ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ በዚህም ፈረንሳይ ዴንማርክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነጥቧን ወደ ስድስት ከፍ አድርጋለች፡፡ የፈረንሳይን የማሸነፊያ ጎሎች ክሊያን ምባፔ በ61ኛው እና 86ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል፡፡ ዴንማርክን…

ፖላንድ ሳዑዲ ዓረቢያን 2 ለ 0 አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ በምድብ ሶስት የሚገኙት ፖላንድ እና ሳዑዲ ዓረቢያ የሁለተኛ ዙር ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ በዚህም ፖላንድ ሳዑዲ ዓረቢያን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነጥቧን ወደ አራት ከፍ ማድረግ ችላለች፡፡ በተቃራኒው በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ጥሩ ተንቀሳቅሳ አርጀንቲናን ያሸነፈችው ሳዑዲ…