Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የቻን ውድድር የምድብ ድልድል መስከረም 21 ቀን ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን (ቻን) ውድድር መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋ ይሆናል፡፡ በ2023 በአልጄሪ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የቻን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳታፊዎችን ቁጥር ያደገ ሲሆን በ18 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ከጥር 5 እስከ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይከናወናል፡፡ በየቀጠናው በተከናወኑ የማጣሪያ ውድድሮች ሞሮኮ፣ ሊቢያ፣ ሴኔጋል፣ ሞሪታኒያ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ጋና፣ አይቮሪኮስት፣ ኮንጎ፣ ዴሞከራቲክ  ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ካሜሩን፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣…
Read More...

ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ከነማ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾመዋል። አሰልጣኙ ፊፋ ለቴክኒክ ባለሙያነት ያቀረባቸውን መመዘኛዎች በማለፍ እንደ ሁኔታው በሚታደስ የሁለት ዓመት ኮንትራት የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነዋል። ኢንስትራክተር አብርሃም በአፍሪካ ከፍተኛ ኢንስትራክተርነት ፣ በአፍሪካ…

ፋሲል ከነማ ቡማሙሩን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪከ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ ከቡሩንዲው ክለብ ቡማሙሩ ጋር የተጫወተው ፋሲል ከነማ 3 ለ ዐ አሸንፏል። በባህርዳር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አለም ብርሃን ይግዛው፣ፈቃዱ አለሙ እና ታፈሰ ሰለሞን የማሸነፊያ ጎሎችን አስቆጥረዋል። የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ መስከረም 6 ቀን የሚደረግ ይሆናል።

ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል።   

በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የሽልማት መርሐ ግብር ላይ አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች እንዳስመዘገቡት ውጤት ከአምስት ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር የሚደርስ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የኢትዮ - ኤሌክትሪክ አትሌት የሆነችውና በ18ኛው የኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ ያስገኘችው ጎቲቶም ገብረስላሴ ልዩ ተሸላሚ…

ፋሲል ከነማ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከቡሩንዲው ቡማሙሩ ጋር ዛሬ ያደርጋል

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከብሩንዲው ቡማሙሩ ጋር ዛሬ ያደርጋል፡፡ የሁለቱ ክለቦች የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰአት ላይ የሚደረግ ይሆናል። በፋሲል ከነማ በኩል ሀብታሙ ተከስተ በህመም ምክንያት ከዛሬው ጨዋታ ውጭ…

ቼልሲ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሼልን አሰናበተ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ቼልሲ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሼልን ማሰናበቱን አስታወቀ። ክለቡ ከትናንት ምሽቱ የዳይናሞ ዛግሬቭ የቻምፒየንስ ሊግ ሽንፈት በኋላ አሰልጣኙን ማሰናበቱን አስታውቋል። አዲሱ የክለቡ ባለቤት ቴድ ቦህሊ የአሰልጣኞች ቡድን አባላትን ክለቡን እንዲመሩ በጊዜያዊነት ተክተዋቸዋል። የ49 አመቱ ጀርመናዊ…

የታዳጊ ወጣቶች ውሃ ዋና ሻምፒዮና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ  ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን  አዘጋጅነት  ከነሀሴ 27 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የ2014 ዓ.ም  የታዳጊ ወጣቶች ውሃ ዋና ሻምፒዮና ተጠናቋል ። በዚኅም የ2014 ዓ.ም የተደጊ ወጣቶች  የውሃ ዋና  ሻምፒዮና ከ14 ዓመት  በታች አዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር  በወንድ እና በሴት የዋንጫ ተሸላሚ …